ኢትዮ-አሜሪካ አትሌቲክስ ማኅበር

Ethio-American Athletics Association

Run for Your Health
Fast as Wind
More Website Templates TemplateMonster.com - April 21, 2014!
ካላንደር / Calendar
Ethio-American Mother's Day 8K
Members
ማኅበሩ አንድ ዓይነት መደብ ያለው የአባላት ስብስብ ሲኖሩት ሁሉም አባል እኩል መብትና ግዴታ ይኖሩታል። Members ለተጨማሪ መረጃ
ጀግኖቻችን / Heroes

እንኳን ደህና መጡ / Welcome

እንኳን ወደ ኢትዮ አሜሪካን አትሌቲክስ ማኅበር ድረ ገፅ በሰላም መጡ።

እኛ በሰሜን አሜሪካና አካባቢዋ የምንገኝ የቀድሞ ነባር አሰልጣኞችና አትሌቶች በአንድነት በመሆን ኢትዮ አሜሪካን አትሌቲክስ ማኅበርን መስርተናል። ይህም ማኅበር ከዘር፣ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ የነፃ ስፖርታዊ ማኅበር ሲሆን ማኅበሩም የረጅምና የአጭር ጊዜ ዓላማ የያዘና አትራፊ ያልሆነ ማኅበር ነው።

ይህ ማኅበር በ2009ዓም ሲመሰረት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመባል ይታወቅ ነበር። ፌዴሬሽኑም በዚህ በምንኖርበት በሀገረ አሜሪካ ያለውን የአትሌቲክስ ሞያ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጭምር ዘወትር ቅዳሜ በተለመደው የስፖርት ማዘውተርያ ሜዳ ላይ በመገኘት ልምምድ በመስጠት ላይ ይገኛል። ፌዴሬሽኑም የ5 ና የ8 ኪሎሜትር ውድድር ላለፉት አራት አመታት እንዳዘጋጀ ይታወቃል። በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚለውን ስያሜ በአባላቱ ጥያቄ መሰረት በዲሲ ሕግና ደንብ መሰረት ከ2014 ዓም ጀምሮ በአዲስ መልክና በአዲስ ስያሜ ትርፋማ ባልሆነ ድርጅት ስም ተመዝግቦ የተለመደውን ዓመታዊ የእናቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ የ8 ኪሎሜትር ውድድርን በየአመቱ በግንቦት ወር ላይ ሲያከብር ቆይቷል በቀጣይም ያከብራል። በተጨማሪም በየሳምንቱ ቅዳሜ ለአትሌቲክስ ፍላጎት ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶችን በማሰባሰብ መሰረታዊ የስልጠና እገዛ በማኅበሩ ነባር አሰልጣኞችና ታዳጊ አሰልጣኞች ስልጠናውን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ጠቃሚ ገፆች / Links